Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy




ነህምያ 7:6
10 Cross References  

ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል።


በሜ​ዶን አው​ራጃ ባለው ባሪ በሚ​ባል ከተማ በን​ጉሡ ቤት ውስጥ አንድ ጥቅ​ልል ተገኘ፤ በው​ስ​ጡም ይህ ነገር ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ተጽፎ ነበር።


የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።


እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከአ​ዛ​ር​ያስ፥ ከረ​ዓ​ምያ፥ ከሄ​ሜ​ኔስ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ል​ሰማ፥ ከሚ​ስ​ፌ​ሬት፥ ከዕ​ዝራ፥ ከበ​ጉ​ዋይ፥ ከነ​ሑም፥ ከበ​ዓና፥ ከመ​ስ​ፈር ጋር መጡ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ የወ​ን​ዶች ቍጥር ይህ ነው፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements