Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ደግ​ሞም፦ ንጉሥ በይ​ሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይና​ገሩ ዘንድ ነቢ​ያ​ትን አቁ​መ​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሡ ይህን ቃል ያወ​ሩ​ለ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ መጥ​ተህ በአ​ን​ድ​ነት እን​ማ​ከር።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለ አንተም ‘በአይሁድ ንጉሥ አለ’ ብለው በኢየሩሳሌም የሚያውጁ ነቢያትን እንኳ ሳይቀር እንደ ሾምህ ተወርቷል፤ ይህም ነገር ለንጉሡ መድረሱ አይቀርም፤ ስለዚህ መጥተህ በአንድነት እንመካከር።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ‘ንጉሥ በይሁዳ አለ’ ብለው ስለ አንተ በኢየሩሳሌም እንዲናገሩ ነቢያትን ሾመሃል፤ አሁንም ይህን ነገር በንጉሡ ዘንድ ይሰማል፤ ስለዚህ መጥተህ በአንድነት እንመካከር።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የይሁዳ ንጉሥ መሆንህንም በኢየሩሳሌም አንዲያውጁ፥ ነቢያት መሾምህን ጌሼም ጨምሮ ነግሮኛል፤ ይህንንም ወሬ ንጉሠ ነገሥቱ እንደሚሰማ የተረጋገጠ ነው፤ ስለዚህ አንተና እኔ ተገናኝተን በጒዳዩ ላይ ብንወያይበት ይሻላል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ደግሞም፦ ንጉሥ በይሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ ነቢያትን አቁመሃል፥ አሁንም ለንጉሡ ይህን ቃል ያወሩለታል፥ እንግዲህ መጥተህ በአንድነት እንማከር የሚል ክፍት ደብዳቤ ነበረ።

See the chapter Copy




ነህምያ 6:7
10 Cross References  

አሁ​ንም እና​ንተ ከሸ​ን​ጎው ጋር ወደ ሻለ​ቃው ሂዱና የም​ት​መ​ረ​ም​ሩ​ትና የም​ት​ጠ​ይ​ቁት አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጣው ንገ​ሩት፤ እኛ ግን ወደ እና​ንተ ከመ​ድ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ገ​ድ​ለው ቈር​ጠ​ናል።”


በዚ​ያም ካህኑ ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቀብ​ተው ያን​ግ​ሡት፤ መለ​ከ​ትም ነፍ​ታ​ችሁ፦ ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ በሉ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ መን​ገሡ ነው፤ አን​ተም ጌታዬ ንጉሥ ይህን አታ​ው​ቅም፤


ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።


“አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል።


እኔም፥ “አንተ ከል​ብህ ፈጥ​ረ​ኸ​ዋል እንጂ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ነገር አይ​ደ​ለም” ብዬ ላክ​ሁ​በት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements