Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እኔም፥ “ለአ​ሕ​ዛብ የተ​ሸ​ጡ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንን አይ​ሁ​ድን በፈ​ቃ​ዳ​ችን ተቤ​ዠን፤ እና​ን​ተስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ች​ሁን? እነ​ር​ሱስ ለእኛ የተ​ሸጡ ይሆ​ና​ሉን?” አል​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ መል​ስም አላ​ገ​ኙም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ለአሕዛብ ተሽጠው የነበሩትን አይሁድ ወንድሞቻችንን በተቻለን ሁሉ ተቤዥተናቸዋል፤ አሁንም እናንተ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁ፤ ይህም መልሰን እንድንቤዣቸው ለማድረግ ብቻ ነው!” አልኋቸው፤ እነርሱም የሚመልሱት አልነበራቸውምና ዝም አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “ለአሕዛብ የተሸጡትን አይሁድ ወንድሞቻችንን በተቻለን መጠን ተቤዠን፥ እናንተ ደግሞ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁ? እነርሱስ ለእኛ ይሸጣሉን? እነርሱም ዝም አሉ፥ የሚመልሱትንም ቃል አጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እኔም፦ ለአሕዛብ የተሸጡትን ወንድሞቻችንን አይሁድን በፈቃዳችን ተቤዠን፥ እናንተስ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁን? እነርሱስ ለእኛ የተሸጡ ይሆናሉን? አልኋቸው። እነርሱም ዝም አሉ፥ መልስም አላገኙም።

See the chapter Copy




ነህምያ 5:8
14 Cross References  

ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ደካማ ወን​ድም አን​ተን በማ​የት ይጎ​ዳል።


በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን?


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፤ ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።


ለእያንዳንዱ እንደ ዐቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።


የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ።


“እና​ንተ ፈራ​ችሁ፥ ዳግ​መ​ኛም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም ቁም ነገር ጠፋ።


የሰ​ሙ​ኝም ብፁዕ ይሉ​ኛል። ምላ​ሳ​ቸ​ውም በት​ና​ጋ​ቸው ተጠጋ።


“ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ሰ​ድብ በሞት ይቀጣ።


እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements