Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ለአ​ንድ ቀን አንድ በሬና ስድ​ስት የሰቡ በጎች፥ አንድ ፍየ​ልም፥ በዐ​ሥር በዐ​ሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይ​ነት ወይን ጠጅ ይዘ​ጋ​ጅ​ልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ዛዝ በሕ​ዝቡ ላይ ከብዶ ነበ​ርና ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​ሻም ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በየዕለቱም አንድ በሬ፣ ስድስት ምርጥ በጎችና የተወሰኑ ወፎች፣ በየዐሥሩም ቀን ብዛት ያለው ልዩ ልዩ የወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር። ይህም ሁሉ ሆኖ ለአንድ አገረ ገዥ የተመደበውን ምግብ ከቶ ጠይቄ አላውቅም፤ በሕዝቡ ላይ የተጣለው ሸክም ከባድ ነበርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ለአንድ ቀን ይሠራ የነበረው አንድ በሬ፥ ስድስት የተመረጡ በጎች ነበር፤ ዶሮዎችም ይዘጋጁልኝ ነበር፥ በየዐሥር ቀኑም ብዛት ያለው ልዩ ልዩ ዓይነት ወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር፤ ይህም ሆኖ ግን የንጉሡን ምግብ አልሻም ነበር በዚህ ሕዝብ ላይ ሥራው ከብዶ ነበርና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በየዕለቱ አንድ በሬ፥ ስድስት ምርጥ በጎችና ብዙ ዶሮች ታርደው ይዘጋጁልኝ ነበር፤ በተጨማሪም በየዐሥር ቀን አንድ ጊዜ የወይን ጠጅ ግብዣ አደርግላቸው ነበር፤ ነገር ግን በሕዝቡ ላይ የተጣለውን ከባድ ሸክም ስለማውቅ፥ ለአገረ ገዢነት የሚገባውን አበል አልጠየቅሁም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከወፎችም በቀር ለአንድ ቀን አንድ በሬና ስድስት የሰቡ በጎች፥ በአሥር በአሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት ወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር፥ ነገር ግን አገዛዝ በሕዝቡ ላይ ከብዶ ነበርና ለአለቃ የሚገባውን ስንቅ አልሻም ነበር።

See the chapter Copy




ነህምያ 5:18
6 Cross References  

አቤቱ፥ አንተ አት​ጣ​ለኝ፤ አም​ላኬ፥ ከእኔ አት​ራቅ።


ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ በዙ​ሪ​ያው ስለ ነበረ ጦር​ነት አባቴ ዳዊት ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት መሥ​ራት እን​ዳ​ል​ቻለ አንተ ታው​ቃ​ለህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements