Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነ​ር​ሱም፥ “እን​መ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም አን​ሻም፤ እን​ደ​ተ​ና​ገ​ርህ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ። ካህ​ና​ቱ​ንም ጠርቼ እን​ደ​ዚህ ነገር ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ል​ኋ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነርሱም፣ “እንመልሳለን፤ ምንም ዐይነት ትርፍ አንጠይቃቸውም፤ እንዳልኸን እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱን ጠራኋቸው፤ መኳንንቱንና ሹማምቱም የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ አማልኋቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነርሱም፦ “እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንፈልግም፤ አንተ እንዳልኸው እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ ቃል እንደገቡት እንዲያደርጉ አስማልኳቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 መሪዎቹም “እንዳዘዝከን እናደርጋለን፤ የተወሰደባቸውን ሀብትና ንብረት ሁሉ እንመልስላቸዋለን፤ የተበደሩትንም ዕዳ ክፈሉ ብለን አንጠይቃቸውም” ሲሉ መለሱልኝ። እኔም ካህናቱን ወደ ውስጥ ጠርቼ፥ መሪዎቹ የገቡትን ቃል ይፈጽሙ ዘንድ እንዲያስምሉአቸው አደረግሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነርሱም፦ እንመልስላቸዋለን፥ ከእነርሱም ምንም አንሻም፥ እንደ ተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው።

See the chapter Copy




ነህምያ 5:12
15 Cross References  

ዕዝ​ራም ተነሣ፤ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ እን​ደ​ዚህ ቃል ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ።


ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።”


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።


ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እንደ ተና​ገ​ር​ኸን እና​ደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባ​ናል።


እር​ሻ​ቸ​ውን፥ የወ​ይ​ና​ቸ​ው​ንና የወ​ይ​ራ​ቸ​ውን ቦታ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የወ​ሰ​ዳ​ች​ሁ​ትን ገን​ዘ​ቡ​ንና እህ​ሉን፥ ወይን ጠጁ​ንና ዘይ​ቱን እባ​ካ​ችሁ ዛሬ መል​ሱ​ላ​ቸው።”


ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም ለም​ድር አሕ​ዛብ አን​ሰ​ጥም፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለል​ጆ​ቻ​ችን አን​ወ​ስ​ድም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements