Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሻ​ቸ​ውን፥ የወ​ይ​ና​ቸ​ው​ንና የወ​ይ​ራ​ቸ​ውን ቦታ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የወ​ሰ​ዳ​ች​ሁ​ትን ገን​ዘ​ቡ​ንና እህ​ሉን፥ ወይን ጠጁ​ንና ዘይ​ቱን እባ​ካ​ችሁ ዛሬ መል​ሱ​ላ​ቸው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዕርሻቸውን፣ የወይንና የወይራ ዘይት ተክል ቦታቸውንና ቤታቸውን በቶሎ መልሱላቸው፤ እንዲሁም የምታስከፍሏቸውን የገንዘቡን፣ የእህሉን፣ የአዲሱን ወይንና ዘይት አንድ መቶኛ ዐራጣ መልሱላቸው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በብድር የያዛችሁትን እርሻቸውን፥ የወይን ቦታቸውን፥ ወይራቸውን፥ ቤታቸውን፥ ከመቶ አንድ የወሰዳችሁትን ብር፥ እህሉን፥ አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይት እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ገንዘብም ሆነ እህል ወይም ወይንና የወይራ ዘይት ቢሆን ያበደራችሁትን ሁሉ ወለዱን ተዉላቸው፤ እርሻቸውን የወይንና የወይራ ዘይት ተክላቸውንና ቤታቸውን ሁሉ አሁኑኑ መልሱላቸው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሻቸውንና ወይናቸውን ወይራቸውንና ቤታቸውንም ከእነርሱም የወሰዳችሁትን ገንዘቡንና እህሉን፥ ወይን ጠጁንና ዘይቱን ከመቶ እጅ አንድ እጅ እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።

See the chapter Copy




ነህምያ 5:11
9 Cross References  

ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው።


እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ይህን አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ አላ​ዘ​ነ​ምና ስለ አን​ዲቱ በግ አራት አድ​ርጎ ይመ​ልስ” አለው።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ያል​ሞ​ላ​ሃ​ቸ​ው​ንም ሀብ​ትን የሞሉ ቤቶች፥ ያል​ማ​ስ​ሃ​ቸ​ው​ንም የተ​ማሱ ጕድ​ጓ​ዶች፥ ያል​ተ​ከ​ል​ሃ​ቸ​ው​ንም ወይ​ንና ወይራ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ በበ​ላ​ህና በጠ​ገ​ብ​ህም ጊዜ፤


እኔ ደግሞ፥ ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ገን​ዘ​ብና እህል ለእ​ነ​ርሱ አበ​ድ​ረ​ናል፤ እባ​ካ​ችሁ፥ ይህን ወለድ እን​ተ​ው​ላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “እን​መ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም አን​ሻም፤ እን​ደ​ተ​ና​ገ​ርህ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ። ካህ​ና​ቱ​ንም ጠርቼ እን​ደ​ዚህ ነገር ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ል​ኋ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements