Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ቅጥ​ሩ​ንም ሠራን፤ ቅጥ​ሩም ሁሉ እስከ እኩ​ሌ​ታው ድረስ ተጋ​ጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበ​ርና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕዝቡ ከልቡ ስለሚሠራ፣ ቅጥሩን እኩሌታው ድረስ መልሰን ሠራነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በአጠገባቸው የተቀመጡ አይሁድ መጥተው፦ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል” ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኛም ቅጽሩን መልሶ የማነጹን ሥራ ቀጠልን፤ ሕዝቡ በትጋት በመሥራቱ ሥራው እየተፋጠነ ሄዶ ግማሽ ደረሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ቅጥሩንም ሠራን፥ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፥ የሕዝቡም ልብ ለሥራው ጨከነ።

See the chapter Copy




ነህምያ 4:6
13 Cross References  

ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።


የሰ​ላም አም​ላክ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን በእ​ና​ንተ እያ​ደ​ረገ ፈቃ​ዱን ታደ​ርጉ ዘንድ በመ​ል​ካም ሥራ ሁሉ ፍጹ​ማን ያድ​ር​ጋ​ችሁ፤ ለእ​ርሱ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ቅጥ​ሩም በኤ​ሉል ወር በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በአ​ምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨ​ረሰ።


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


ከዚ​ህም በላይ ደግሞ የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ስለ ወደ​ድሁ፥ ለመ​ቅ​ደሱ ከሰ​በ​ሰ​ብ​ሁት ሁሉ ሌላ የግል ገን​ዘቤ የሚ​ሆን ወር​ቅና ብር አለ​ኝና እነሆ፥ ለአ​ም​ላኬ ቤት ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስና ሕዝ​ቡም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ስላ​ዘ​ጋ​ጀው ነገር ደስ አላ​ቸው። ይህ ነገር በድ​ን​ገት ተደ​ር​ጎ​አ​ልና።


በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አት​ክ​ደን፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከፊ​ትህ አይ​ደ​ም​ሰስ፤ በሠ​ራ​ተ​ኞች ፊት አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ሃ​ልና።


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤ ስድ​ብን እጅግ ጠግ​በ​ና​ልና፤


እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements