Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰንባላጥ ቅጥሩን እንደምንሠራ በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ እጅግም ተበሳጨ። በአይሁድም ላይ ተሣለቀ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሳንበላጥ፥ ጦብያ፥ ዓረባውያን፥ አሞናውያንና አሽዶዳውያን የሚታደሰው የኢየሩሳሌም ቅጥር ከፍ እያለ እንደ ሄደ፥ የፈረሰውም እየተጠገነ እንደሆነ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እኛ አይሁድ የቅጽሩን ግንብ ሥራ መጀመራችንን ሰንባላጥ በሰማ ጊዜ በጣም ተቈጣ፤ ተበሳጭቶም ሊዘባበትብን ተነሣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ።

See the chapter Copy




ነህምያ 4:1
13 Cross References  

የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።


ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ቅጥ​ሩም በኤ​ሉል ወር በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በአ​ምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨ​ረሰ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙ​ሪ​ያ​ችን የነ​በሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ፈሩ፤ አይ​ተ​ውም እጅግ ተደ​ና​ገጡ፤ ይህም ሥራ በአ​ም​ላ​ካ​ችን እንደ ተፈ​ጸመ አወቁ።


ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን በኰ​በ​ለሉ በአ​ይ​ሁድ እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ኛል፤ እነ​ር​ሱም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል ብዬ እፈ​ራ​ለሁ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements