Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኛው የሐ​ሬ​ህያ ልጅ ዑዝ​ኤል ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም ከሽቱ ቀማ​ሚ​ዎች የነ​በረ ሐና​ንያ ሠራ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጠገኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ የሆነው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል የሚቀጥለውን ክፍል ሠራ፤ ከሽቱ ቀማሚዎች አንዱ የሆነው ሐናንያ ደግሞ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። እነርሱም ሰፊው ቅጥር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ኢየሩሳሌምን መልሰው ሠሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዚኤል አደሰ። በአጠገቡም የሽቶ ቀማሚዎች ልጅ ሐናንያ አደሰ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን አደሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ወርቅ አንጣሪው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። ቀጥሎ ያለውንም ክፍል ሽቶ ቀማሚው ሐናንያ ሠራ፤ እነዚህ ሰዎች ኢየሩሳሌምን “ሰፊው ቅጽር” ተብሎ እስከሚጠራው ስፍራ ድረስ ያለውን ሁሉ ሠሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል አደሰ። በአጠገቡም ከሽቱ ቀማሚዎች የነበረ ሐናንያ አደሰ፥ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን ጠገኑ።

See the chapter Copy




ነህምያ 3:8
6 Cross References  

ሁለ​ተ​ኛ​ውም የአ​መ​ስ​ጋ​ኞቹ ክፍል ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ነበ​ርን፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ፥ በእ​ቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥


ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።


የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።


በቀ​ማ​ሚም ብል​ሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሆ​ናል።


ዮሴ​ፍም ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች አገ​ል​ጋ​ዮቹ አባ​ቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም እስ​ራ​ኤ​ልን በሽቱ አሹት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements