ነህምያ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በአጠገባቸውም ቴቁሓውያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላላቆቻቸው ግን ለሥራው አንገታቸውን አላዋረዱም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሔ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንታቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በአጠገባቸውም ቴቁአውያን አደሱ፤ መኳንንቶቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አልሰጡም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በአጠገባቸውም ቴቁሐውያን አደሱ፥ ታላላቆቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አላዋረዱም። See the chapter |