Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል) የመሼዛቤል የልጅ ልጅ የሆነው የበራክያ ልጅ መሹላም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚገኘውን ክፍል የበዓና ልጅ ሳዶቅ ሠራው። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል)

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በአጠገባቸውም የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም አደሰ። በአጠገባቸውም የበዓና ልጅ ሳዶቅ አደሰ።

See the chapter Copy




ነህምያ 3:4
11 Cross References  

በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃ​ዎ​ቹም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት በካ​ህኑ በኦ​ርያ ልጅ በሜ​ሪ​ሞት እጅ ተመ​ዘኑ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን የኢ​ያሱ ልጅ ኢዮ​ዛ​ብ​ድና የቤ​ንዊ ልጅ ናሕ​ድያ ነበሩ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ከኤ​ል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ጀምሮ እሰከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መጨ​ረሻ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።


ቡኒ፥ ዓዝ​ጋድ፥ ቤባይ፤


ሜሱ​ላም፥ አብ​ድያ፥ ሚያ​ሚን፤


የአ​ስ​ናሃ ልጆ​ችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ቴቁ​ሓ​ው​ያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸው ግን ለሥ​ራው አን​ገ​ታ​ቸ​ውን አላ​ዋ​ረ​ዱም።


ሜሴ​ዜ​ቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፤


ከካ​ህ​ና​ቱም ልጆች፤ የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ።


ጦብያ የአ​ራሄ ልጅ የሴ​ኬ​ንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐ​ናን የቤ​ራ​ክ​ያን ልጅ የሜ​ሱ​ላ​ምን ሴት ልጅ ስላ​ገባ፥ በይ​ሁዳ ብዙ ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ተማ​ም​ለው ነበ​ርና።


ከካ​ህ​ና​ቱም የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ሙም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements