Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ደ​ዚህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? አም​ላ​ካ​ች​ንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ኛና በዚች ከተማ ላይ አም​ጥቶ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እና​ን​ተስ ሰን​በ​ትን በማ​ር​ከ​ሳ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መዓ​ትን ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የቀድሞ አባቶቻችሁ ያደረጉት ይህንኑ አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ሁሉ ጥፋት በእኛና በዚች ከተማ ላይ ያመጣው በዚሁ በደላችን አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን በማርከስ የባሰ መከራ በእስራኤል ላይ ታመጣላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አምላካችን በእኛና በከተማይቱ ላይ ይህን ጥፋት ያመጣው የቀድሞ አባቶቻችሁ ይህን ጥፋት ስላደረጉ አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን ባለማክበራችሁ የእግዚአብሔርን ቊጣ በእስራኤል ላይ ታነሣሣላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው።

See the chapter Copy




ነህምያ 13:18
16 Cross References  

ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፍ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ።


በግ​ብ​ፅም የነ​በ​ረ​ውን ዝሙ​ቷን አል​ተ​ወ​ችም፤ በዚ​ያም በኮ​ረ​ዳ​ነቷ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኝ​ተው ነበር፤ የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋ​ንም ጡቶች ዳብ​ሰው ነበር፤ ዝን​የ​ታ​ቸ​ው​ንም አፍ​ስ​ሰ​ው​ባት ነበር።


በውኑ በይ​ሁዳ ምድ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያደ​ረ​ጉ​ትን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ክፋት፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት ክፋት፥ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ክፋት የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ክፋት ረስ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልን?።


ነገር ግን የሰ​ን​በ​ትን ቀን እን​ድ​ት​ቀ​ድሱ፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክ​ምን ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች እን​ዳ​ት​ገቡ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ባት​ሰ​ሙኝ፥ በበ​ሮ​ችዋ ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ግን​ቦች ትበ​ላ​ለች፤ አት​ጠ​ፋ​ምም።


እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እስ​ከ​ዚ​ህም ድረስ ባት​ሰ​ሙኝ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ በቅ​ጣ​ታ​ችሁ ላይ ሰባት እጥፍ መቅ​ሠ​ፍ​ትን እጨ​ም​ራ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሥ​ራ​ች​ሁን ክፋ​ትና ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ርኵ​ሰት ይታ​ገሥ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚህ ምድ​ራ​ችሁ ባድማ፥ በረ​ሃና መረ​ገ​ሚያ ሆና​ለች፤ እስከ ዛሬም የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።


ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት ሥራ ሁሉ በየ​ዓ​መቱ የሰ​ቅል ሢሶ እና​መጣ ዘንድ ሥር​ዐት በራ​ሳ​ችን ላይ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements