Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ለባሪያህ ለሙሴ እንዲህ ስትል የሰጠኸውን ቃል ዐስብ፤ ‘ታማኞች ካልሆናችሁ፣ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለአገልጋይህ ለሙሴ እንዲህ ብለህ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ። “ታማኞች ካልሆናችሁ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8-9 ‘እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እኔን በእምነት ባትከተሉ በአረማውያን ሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያዘዝኳችሁን ትእዛዞች ብትፈጽሙ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የተበታተናችሁ ብትሆኑም እንኳ ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ወደ መረጥሁት ስፍራ እንደገና በመሰብሰብ መልሼ አመጣችኋለሁ’ ስትል ለሙሴ የተናገርከውን ቃል አስብ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8-9 አሁንም፦ ‘ብትተላለፉ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ወደ እኔ ብትመለሱ ግን ትእዛዜንም ብትጠብቁ ብታደርጓትም፥ ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ምንም ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ’ ብለህ ለባሪያህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ።

See the chapter Copy




ነህምያ 1:8
10 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድር ዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ይበ​ት​ን​ሃል፤ በዚ​ያም አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት፥ እን​ጨ​ት​ንና ድን​ጋ​ይን ታመ​ል​ካ​ለህ።


ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ።


ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል።


ስለ​ዚህ በመ​ካ​ከ​ልሽ አባ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ልጆ​ችም አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ ፍር​ድ​ንም አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ረ​ውን ሁሉ ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ።


“ነገር ግን በሀ​ገ​ሮች በተ​በ​ተ​ና​ችሁ ጊዜ ከእ​ና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ጦር የዳ​ኑ​ትን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements