Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ናሆም 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣ አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤ ይህች የጠንቋዮች እመቤት በዝሙቷ አሕዛብን፣ በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፤ እርሷም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይህም የሆነው ገደብ በሌለው የአምንዝራይቱ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርስዋ በመተት እመቤትነትና በቊንጅናዋ የምታታልልና መንግሥታትን በዝሙትዋ፥ ሕዝቦችን በጥንቈላዋ የምትማርክ ነች።

See the chapter Copy




ናሆም 3:4
10 Cross References  

አሁን ግን በአ​ንድ ቀን እነ​ዚህ ሁለት ነገ​ሮች በድ​ን​ገት ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ትና መበ​ለ​ት​ነት ስለ መተ​ቶ​ችሽ ብዛ​ትና ስለ አስ​ማ​ቶ​ችሽ ጽናት ፈጽ​መው ይመ​ጡ​ብ​ሻል።


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤


“ስለ​ዚህ ዘማ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements