Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢየሱስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያው ተቀምጦ አየና፣ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሳለ ማቴዎስ የተባለውን ቀራጭ በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ!” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 9:9
16 Cross References  

እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥


በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።


ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በደ​ረሱ ጊዜ ጴጥ​ሮስ፥ ዮሐ​ንስ፥ ያዕ​ቆብ፥ እን​ድ​ር​ያስ፥ ፊል​ጶስ፥ ቶማስ፥ ማቴ​ዎስ፥ በር​ተ​ሎ​ሜ​ዎስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆብ፥ ቀና​ተ​ኛው ስም​ዖን፥ የያ​ዕ​ቆብ ልጅ ይሁ​ዳም ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በት ሰገ​ነት ወጡ።


ማቴ​ዎ​ስና ቶማስ፥ የእ​ል​ፍ​ዮስ ልጅ ያዕ​ቆ​ብና ቀናዒ የሚ​ባ​ለው ስም​ዖን።


ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥


አሁ​ንም ይህች ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ግብ​ርና ቀረጥ መጥ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መን​ግ​ሥ​ትን ይጐ​ዳል።


ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።


በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።


እነዚያንም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ፤’ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements