ማቴዎስ 9:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “እኛና ፈሪሳውያን ስንጾም፣ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ለምን አይጾሙም?” ብለው ጠየቁት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” አሉት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በዚያን ጊዜ፥ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “እኛና ፈሪሳውያን ዘወትር እንጾማለን፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት። See the chapter |