Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 6:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?

See the chapter Copy




ማቴዎስ 6:26
15 Cross References  

ለሌ​ሎች አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም፥ ፍር​ዱ​ንም አል​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውም።


ልጆቹ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲጮኹ፥ የሚ​በ​ሉ​ትም ፈል​ገው ሲቅ​በ​ዘ​በዙ፥ ለቍራ መብ​ልን የሚ​ሰ​ጠው ማን ነው?


ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።


ወይስ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?


እር​ሱም ከም​ድር እን​ስ​ሶች ይልቅ፥ ከሰ​ማ​ይም ወፎች ይልቅ የሚ​ለ​የኝ ነው።


ከፊ​ትህ አት​ጣ​ለኝ፥ ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህ​ንም ከእኔ ላይ አት​ው​ሰ​ድ​ብኝ።


እር​ሱም አለ፦ እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጎተ​ራ​ዬን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ጎተ​ራም እሠ​ራ​ለሁ፤ እህ​ሌ​ንና በረ​ከ​ቴ​ንም በዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ።


ከሚ​በ​ላ​ውም የመ​ብል ዓይ​ነት ሁሉ ለአ​ንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ እር​ሱም ለአ​ንተ፥ ለእ​ነ​ር​ሱም መብል ይሆ​ናል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements