Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ተፉበትም፤ መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ተፉበትም፤ የሸንበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱን መቱት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ተፉበት፤ መቃውንም ነጥቀው ራሱን መቱት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ምራቃቸውንም ይተፉበት ነበር፤ ዘንጉንም ከእጁ ወስደው ራስ ራሱን ይመቱት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:30
12 Cross References  

ጀር​ባ​ዬን ለግ​ር​ፋት፥ ጕን​ጬ​ንም ለጽ​ፍ​ዐት ሰጠሁ፤ ፊቴ​ንም ከም​ራቅ ኀፍ​ረት አል​መ​ለ​ስ​ሁም።


በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፤ ሌሎችም በጥፊ መትተው “ክርስቶስ ሆይ! በጥፊ የመታህ ማን ነው?


ራሱንም በመቃ መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።


እርሱ ግን በመ​ከ​ራው ጊዜ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም፤ እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሸ​ላ​ቾቹ ፊት ዝም እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


ይዘብቱበትማል፤ ይተፉበትማል፤ ይገርፉትማል፤ ይገድሉትማል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።


አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና “ትንቢት ተናገር፤” ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements