Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ጲላጦስ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጲላጦስም፣ “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ይሰቀል!” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጲላጦስም “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ጲላጦስም “ታዲያ፥ መሲሕ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!” ሲሉ መለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ጲላጦስ፦ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም፦ ይሰቀል አሉ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:22
16 Cross References  

እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ በእ​ርሱ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ተስፋ የሰ​ጣ​ች​ሁን ዕወቁ።


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


የካህናት አለቆችም ሸንጎውን ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙምም፤


እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ “በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤


ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።


በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።


“ቤተ ሰቦቼ እኔ ስራ​ራ​ላ​ቸው፥ ሥጋ​ውን እን​በላ ዘንድ ማን በሰ​ጠን ብለው እንደ ሆነ፥


ገዢውም መልሶ “ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም “በርባንን” አሉ።


ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።


ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው።


ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ምንም በደል ባላ​ገ​ኙ​በት ጊዜ እን​ዲ​ገ​ድ​ለው ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements