Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 26:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ሁላችሁም በዚህች ሌሊት በእኔ ተሰናክላችሁ ትሄዳላችሁ፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና፥ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፥ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ ‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ተጽፎአልና በዚህች ሌሊት፥ ሁላችሁም ትክዱኛላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፦ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤

See the chapter Copy




ማቴዎስ 26:31
16 Cross References  

ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።


እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ በየ​ቦ​ታዉ የም​ት​በ​ታ​ተ​ኑ​በት፥ እኔ​ንም ብቻ​ዬን የም​ት​ተ​ዉ​በት ጊዜ ይደ​ር​ሳል፤ ደር​ሶ​አ​ልም፤ እኔ ግን ብቻ​ዬን አይ​ደ​ለ​ሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና።


በተ​ግ​ሣ​ጽህ ስለ ኀጢ​አቱ ሰውን ዘለ​ፍ​ኸው፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ሸረ​ሪት አቀ​ለ​ጥ​ኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።


ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።”


ቆፍ። ወዳ​ጆ​ችን ጠራሁ፤ እነ​ር​ሱም ቸል አሉኝ፤ ካህ​ና​ቶ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ረቱ ዘንድ መብል ሲፈ​ልጉ በከ​ተማ ውስጥ ሳያ​ገኙ አለቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፤” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements