ማቴዎስ 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ስለዚህ የሚነግሯችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እንደሚናገሩት አያደርጉምና ተግባራቸውን አትከተሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ የሚሉአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያደርጉትን አታድርጉ፤ የሚናገሩትን አያደርጉትምና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ስለዚህ እነርሱ የሚሉአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁም፤ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታድርጉ፤ እነርሱ የሚናገሩትን በሥራ ላይ አያውሉትም፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። See the chapter |