Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዚያን ጊዜ ባሮቹን ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ከዚያም ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘የሰርጉ ድግስ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የተጋበዙት የሚገባቸው ሆነው ስላልተገኙ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚያን ጊዜ ባርያዎቹን እንዲህ አላቸው ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ የታደሙት ግን የተገቡ አልሆኑም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘እነሆ፥ የሠርጉ ድግስ ተዘጋጅቶአል፤ የተጠሩት ግን ለግብዣው የተገቡ አልሆኑም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዚያን ጊዜ ባሮቹን፦ ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤

See the chapter Copy




ማቴዎስ 22:8
11 Cross References  

ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።”


ያን ዓለ​ምና የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ሊወ​ርሱ የሚ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚያ ግን አያ​ገ​ቡም፤ አይ​ጋ​ቡም።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ፤’ አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements