Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም። ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በእናንተ መካከል እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ከእናንተ መካከል ታላቅ መሆን የሚፈልግ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በእናንተስ መካከል እንዲህ መሆን አይገባም። ነገር ግን ከእናንተ መካከል ታላቅ መሆን የሚፈልግ የእናንተ አገልጋይ ይሁን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥

See the chapter Copy




ማቴዎስ 20:26
23 Cross References  

በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤


እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


ተቀምጦም ዐሥራ ሁለቱን ጠርቶ “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን፤” አላቸው።


ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ፤


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?’ ይሉታል።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር፤


በዚያን ቀን ከጌታ ምሕረትን እንዲያገኝ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ።


ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ እን​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለን እንጂ እን​ድ​ታ​ምኑ ግድ የም​ን​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ቆማ​ች​ኋ​ልና።


ወደ ሰል​ሚና ሀገ​ርም ገብ​ተው በአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራ​ቦች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ፤ ዮሐ​ን​ስም እየ​አ​ገ​ለ​ገ​ላ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤


በር​ኵ​ሰ​ትሽ ሴሰ​ኝ​ነት አለ፤ አነ​ጻ​ሁሽ፤ አል​ነ​ጻ​ሽ​ምና መዓ​ቴን በላ​ይሽ እስ​ክ​ጨ​ርስ ድረስ እን​ግ​ዲህ ከር​ኵ​ሰ​ትሽ አት​ነ​ጺም።


ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።


ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤


ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ታላቁ እንደ ታናሽ ይሁ​ና​ችሁ፤ አለ​ቃ​ውም እንደ አገ​ል​ጋይ ይሁን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements