Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 20:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ታዲያ በራሴ ገንዘብ የፈለግሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ ቸር በመሆኔ ምቀኛነት ያዘህን?’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በገዛ ገንዘቤ የፈለግኹትን ማድረግ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ ለጋሥ ስለ ሆንኩ አንተ ትመቀኛለህ?’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?

See the chapter Copy




ማቴዎስ 20:15
24 Cross References  

ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የም​ሕ​ረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አል​ሰ​ጠ​ው​ምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በል​ብህ እን​ዳ​ታ​ስብ ለራ​ስህ ዕወቅ። ወን​ድ​ም​ህም ዐይ​ኑን በአ​ንተ ላይ ያከ​ፋል፤ እር​ሱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ላይ ይጮ​ሃል፤ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃል።


ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤


ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር።


እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን።


ማን ይመ​ረ​ም​ር​ሃል? የም​ት​ታ​በ​ይስ በም​ን​ድን ነው? ከሌላ ያላ​ገ​ኘ​ኸው አለ​ህን? ያለ​ህ​ንም ከሌላ ካገ​ኘህ እን​ዳ​ላ​ገኘ ለምን ትኮ​ራ​ለህ?


አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ከስስታም ሰው ጋር አትመገብ፥ ምግቡንም አትመኝ፤


በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በክ​ብሬ በፊ​ትህ አል​ፋ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በፊ​ትህ እጠ​ራ​ለሁ፤ ይቅ​ርም የም​ለ​ውን ይቅር እላ​ለሁ፤ የም​ም​ረ​ው​ንም እም​ራ​ለሁ” አለ።


ወንድሞች ሆይ! እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ፤ እነሆ ፈራጅ በደጅ ፊት ቆሞአል።


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


በኃ​ጢ​አ​ታ​ችን የሞ​ትን ሳለን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወ​ትን ሰጠን፤ በጸ​ጋ​ውም ዳንን።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እን​ደ​ሚ​ሠራ በውኑ እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ መሥ​ራት አይ​ቻ​ለ​ኝ​ምን? እነሆ ጭቃው በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ፥ እን​ዲሁ እና​ንተ በእኔ እጅ አላ​ችሁ።


ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements