Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 13:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዐይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 “ደግሞም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር ተጥሎ የዓሣ ዐይነቶችን የያዘ መረብ ትመስላለች፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 “ደግሞም መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለችና ከሁሉም ዓይነት ዓሣ የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እንዲሁም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለች መረብን ትመስላለች፤ እርስዋ በየዐይነቱ ዓሣ የምትሰበስብ ናት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

See the chapter Copy




ማቴዎስ 13:47
33 Cross References  

በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።


“በሰርዴስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት እንዲህ ይላል “ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ፤ ሞተህማል።


ኢየሱስም “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ፤” አላቸው።


ይኸ​ውም ባሪ​ያ​ዎች ያደ​ር​ጉን ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያገ​ኘ​ና​ትን ነጻ​ነት ሊሰ​ልሉ በስ​ውር ወደ እኛ የገቡ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራ​ንን ደስ አይ​በ​ላ​ቸው ብዬ ነው።


በመ​ን​ገድ ዘወ​ትር መከራ እቀ​በል ነበር፤ በወ​ን​ዝም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ወን​በ​ዴ​ዎ​ችም አሠ​ቃ​ዩኝ፤ ዘመ​ዶ​ችም አስ​ጨ​ነ​ቁኝ፤ አሕ​ዛብ መከራ አጸ​ኑ​ብኝ፤ በከ​ተማ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በበ​ረ​ሃም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በባ​ሕ​ርም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራን መከራ አጸ​ኑ​ብኝ።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ወደ እነ​ርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ ጠማማ ትም​ህ​ር​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ይነ​ሣሉ።


እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው።


እርሱም “በኋላዬ ኑ፤ ሰዎችንም አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው።


ከእ​ና​ንተ የተ​መ​ረ​ጡት ወን​ድ​ሞች ተለ​ይ​ተው እን​ዲ​ታ​ወቁ ትለ​ያዩ ዘንድ ግድ ነው።


በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል።


ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።


“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።


ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።


በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፤ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ፤ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements