Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ሁሉም ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ ሌላ ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድ ራሱ ፈቅዶ ከሚገልጥላቸው ሌላ አብን የሚያውቅ የለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 11:27
21 Cross References  

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”


ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።


ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።


አብ እኔን እን​ደ​ሚ​ያ​ው​ቀኝ እኔም አብን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ለበ​ጎ​ችም ቤዛ አድ​ርጌ ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው በቀር አብን ያየው ማንም የለም፤ እር​ሱም አብን አየው።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


እኔ ግን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እኔ ከእ​ርሱ ነኝና፥ እር​ሱም ልኮ​ኛ​ልና።


“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements