Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 10:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይቀበላል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ይቀበላል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 10:41
27 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱ​ሳ​ንን ስለ አገ​ለ​ገ​ላ​ችሁ፥ እስከ አሁ​ንም ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸው ያደ​ረ​ጋ​ች​ት​ሁን ሥራ፥ በስ​ሙም ያሳ​ያ​ች​ሁ​ትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመ​ፀኛ አይ​ደ​ለ​ምና።


ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


አሁ​ንም የሰ​ው​የ​ውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አን​ተም ይጸ​ል​ያል፤ ትድ​ና​ለ​ህም። ባት​መ​ል​ሳት ግን አንተ እን​ድ​ት​ሞት፥ ለአ​ንተ የሆ​ነ​ውም ሁሉ እን​ዲ​ሞት በር​ግጥ ዕወቅ።”


ይህ​ንስ በፈ​ቃዴ አድ​ር​ጌው ብሆን ዋጋ​ዬን ባገ​ኘሁ ነበር፤ በግድ ከሆነ ግን በተ​ሰ​ጠኝ መጋ​ቢ​ነት አገ​ለ​ገ​ልሁ።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


እኔ​ንና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ሁሉ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​በለ ጋይ​ዮ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ የከ​ተ​ማው መጋቢ አር​ስ​ጦ​ስና ወን​ድ​ማ​ችን ቁአ​ስ​ጥ​ሮ​ስም ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።


ክፉ ምክ​ርን መክ​ረ​ዋ​ልና ለነ​ፍ​ሳ​ቸው ወዮ​ላት! እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጻድ​ቁን እን​ሻ​ረው፤ ሸክም ሆኖ​ብ​ና​ልና፤” ስለ​ዚህ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ፍሬ ይበ​ላሉ።


የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልገውም ያገኛል፤ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።


እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?’ ይሉታል።


ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements