Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ “ሁላችሁ እኔን ስሙ፤ አስተውሉም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙኝ፤ ሁላችሁም አስተውሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙኝ፤ ሁላችሁም አስተውሉ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሕዝቡንም እንደገና ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ሁላችሁም በማስተዋል አዳምጡኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ፦ ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።

See the chapter Copy




ማርቆስ 7:14
14 Cross References  

ሕዝቡንም ጠርቶ “ስሙ አስተውሉም፤


ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው።


እር​ሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስ​ማ​ትን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፥ አታ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ ማየ​ት​ንም ታያ​ላ​ችሁ፥ አት​መ​ለ​ከ​ቱ​ምም” በላ​ቸው አለኝ።


እናንተ የዋሆች፥ ጥበብን አስተውሉ፤ እናንተም ሰነፎች፥ ዕውቀትን ገንዘብ አድርጉ፤


በም​ድረ በዳ እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑ​ትና እን​ዳ​ስ​ቈ​ጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድም​ፁን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።


ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።


በዚ​ያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እስ​ኪ​ረ​ጋ​ገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን እርሾ ተጠ​በቁ፤ ይኸ​ውም ግብ​ዝ​ነት ነው።


ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”


ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።


ይህ​ንም ቃል ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለይ​ሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለተ​ቀ​መጡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements