Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 5:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ፍችውም “አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ!” ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ከዚያም የብላቴናዪቱን እጅ ይዞ፣ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ትርጕሙም፣ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ከዚያም የልጅቱን እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም፥ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 የልጅትዋንም እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ትርጒሙም “አንቺ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ፤” ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ፦ ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 5:41
13 Cross References  

ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።


እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።


“ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው።


ለሚ​ፈ​ሩት ችግር የለ​ባ​ቸ​ው​ምና ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ።


ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወድዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው።


በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናት ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ።


ብላቴናይቱም የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements