Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 5:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ “ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው?” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ወዲያውኑ ኢየሱስ፣ ኀይል ከርሱ እንደ ወጣ ዐውቆ፤ ወደ ሕዝቡ ዘወር በማለት፣ “ልብሴን የነካው ማን ነው?” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ኢየሱስም ወዲያውኑ ኃይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐውቆ፤ ወደ ሕዝቡ ዞሮ፥ “ልብሴን የነካ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ኢየሱስም ወዲያውኑ ኀይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ፤ ወደ ሕዝቡም ዘወር ብሎ፦ “ልብሴን የነካ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ፦ ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።

See the chapter Copy




ማርቆስ 5:30
5 Cross References  

ሕዝቡ ሁሉ ሊዳ​ስ​ሱት ይሹ ነበር፤ ኀይል ከእ​ርሱ ይወጣ ነበ​ርና፥ ሁሉ​ንም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የዳ​ሰ​ሰኝ አለ፤ ከእኔ ኀይል እንደ ወጣ ዐው​ቃ​ለ​ሁና” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


ደቀ መዛሙርቱም “ሕዝቡ ሲያጋፉህ እያየህ ‘ማን ዳሰሰኝ?” ትላለህን?” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements