Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 5:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና ድና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ትንሽዋ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናት፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት!” ሲል አጥብቆ ለመነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 5:23
26 Cross References  

እጁ​ንም በላ​ይዋ ጫነ፤ ያን​ጊ​ዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነ​ችው።


ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወ​ሳ​ቸው።


እባቦችን ይይዛሉ፤የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ።


የፑ​ፕ​ል​ዮ​ስም አባት በን​ዳ​ድና በተ​ቅ​ማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም እርሱ ወዳ​ለ​በት ገብቶ ጸለ​የ​ለት፤ እጁ​ንም በላዩ ጭኖ ፈወ​ሰው።


ከም​ኵ​ራ​ቡም ወጥቶ ወደ ስም​ዖን ቤት ገባ፤ የስ​ም​ዖን አማ​ትም በብ​ርቱ ንዳድ ታማ ነበ​ርና ስለ እር​ስዋ ነገ​ሩት።


ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፤ በዐይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት “አንዳች ታያለህን?” ብሎ ጠየቀው።


ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤


ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ።


ብዙ አጋንንትንም አወጡ፤ ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ፊት አቆ​ሙ​አ​ቸው፤ ጸል​የ​ውም እጃ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ ጫኑ።


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።


በዚያ ጊዜም እጃ​ቸ​ውን ጫኑ​ባ​ቸው፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ተቀ​በሉ።


ሳው​ልም በራ​እይ ሐና​ንያ የሚ​ባል ሰው ወደ እርሱ ገብቶ ያይ ዘንድ እጁን ሲጭ​ን​በት አየ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements