Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 4:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እርሱም ተነሥቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም፣ “ጸጥ፣ ረጭ በል!” አለው። ነፋሱም ጸጥ፣ ረጭ አለ፤ ፍጹምም ጸጥታ ሆነ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ዝም በል፤ ፀጥ በል፤” አለው። ነፋሱም ተወ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 እርሱም ነቅቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል!” አለው፤ ነፋሱ ተወ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።

See the chapter Copy




ማርቆስ 4:39
21 Cross References  

ዘመ​ና​ችን ሁሉ አል​ፎ​አ​ልና፥ እኛም በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትህ አል​ቀ​ና​ልና፤ ዘመ​ኖ​ቻ​ች​ንም እንደ ሸረ​ሪት ድር ይሆ​ናሉ።


በኀ​ይሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዛል፤ ዐይ​ኖቹ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ የም​ታ​ውቁ ራሳ​ች​ሁን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።


በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።


ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥


እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤


እስ​ከ​ዚህ ድረስ ድረሺ፥ ከወ​ሰ​ን​ሽም አት​ለፊ፤ ነገር ግን ማዕ​በ​ልሽ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይገ​ደብ አል​ኋት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና “አንተ ድዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፤ ከእርሱ ውጣ! ከእንግዲህም አትግባበት፤” አለው።


አን​ተም በት​ር​ህን አንሣ፤ እጅ​ህ​ንም በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈ​ለ​ውም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ያል​ፋሉ።


በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው።


ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል።


ካፍ። ጌታ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጥ​ል​ምና፤


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዝም በልና ከእ​ርሱ ውጣ” ብሎ ገሠ​ጸው፤ ጋኔ​ኑም በም​ኵ​ራቡ መካ​ከል ጣለ​ውና ከእ​ርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አል​ጐ​ዳ​ውም።


ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements