Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገ ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሚሠራውን ነገር የሰሙ ሰዎችም ከይሁዳ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከኤዶምያስ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ወደ እርሱ መጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያደረገውን ነገር ሁሉ ሰምተው፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ፥ ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ያደርግ የነበረውንም ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እነርሱም ከገሊላ፥ ከይሁዳ፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር፥ እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ከተሞች የመጡ ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገው ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ።

See the chapter Copy




ማርቆስ 3:8
18 Cross References  

የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤


ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።


ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ። ወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ፤ ሊሰወርም አልተቻለውም፤


ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተቈ​ጠ​ርሁ፥ ረዳ​ትም እን​ደ​ሌ​ለው ሰው ሆንሁ።


ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ ዐሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።


የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።


በደ​ቡ​ብም በኩል በም​ድ​ራ​ቸው ዳርቻ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ድን​በር ያሉት የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቤሴ​ሌ​ኤል፥ አራ፥ አሦር፤


ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements