Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ፤ ይከተሉትም ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በሌዊም ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች ተከትለውት ስለ ነበር፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ዐብረው ይመገቡ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ፤ ይከተሉትም ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በሌዊ ቤት በማእድ ተቀምጦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ተከትለውት ስለ ነበር ከእነርሱ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በገበታ ቀርበው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ ይከተሉትም ነበር።

See the chapter Copy




ማርቆስ 2:15
8 Cross References  

ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ሊሰ​ሙት ወደ እርሱ ይቀ​ርቡ ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና “ተከተለኝ፤” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements