Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 14:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 እርሱ ግን ዝም አለ፤ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና “የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን?” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም። ሊቀ ካህናቱም እንደ ገና፣ “የቡሩኩ ልጅ፣ ክርስቶስ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም። ሊቀ ካህናቱም እንደገና፥ የቡሩኩ ልጅ፥ ክርስቶስ አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 ኢየሱስ ግን ዝም አለ እንጂ ምንም መልስ አልሰጠም። የካህናት አለቃውም “የቡሩክ እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ አንተ ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 14:61
30 Cross References  

ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “አንተ አልህ፤” ብሎ መለሰለት።


እርሱ ግን በመ​ከ​ራው ጊዜ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም፤ እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሸ​ላ​ቾቹ ፊት ዝም እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።


አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ሊሞት ይገ​ባል፤ ራሱን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አድ​ር​ጎ​አ​ልና” አሉት።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነኝ ብላ​ችሁ፥ አብ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ወደ ዓለ​ምም የላ​ከ​ውን እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ? ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ።


እኔም ራሴ አይ​ቻ​ለሁ፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።”


ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” አለ።


እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


በታ​ላቅ ጉባኤ ጽድ​ቅ​ህን አወ​ራሁ፤ እነሆ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድ​ቄን ታው​ቃ​ለህ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።


ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል።


ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።


ደግ​ሞም ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገባና ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ምንም አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው።


አይ​ሁ​ድም እር​ሱን ከብ​በው፥ “እስከ መቼ ድረስ ሰው​ነ​ታ​ች​ንን ታስ​ጨ​ን​ቀ​ና​ለህ? አንተ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆንህ ገል​ጠህ ንገ​ረን” አሉት።


ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶ “አንዳች አትመልስምን? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው?” ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements