Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለ ጦርነትና ጦርነትን የሚያናፍስ ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በአቅራቢያችሁ ጦርነት ሲደረግና በሩቅም የጦርነትን ወሬ ስትሰሙ አትደንግጡ፤ ይህ ሁሉ ሊሆን ግድ ነው፤ ይሁን እንጂ መጨረሻው ገና ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 13:7
17 Cross References  

“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ሞት ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ እን​ዲ​ነሣ፥ እየ​ተ​ረ​ጐ​መና እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፥ “ይህ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው” ይል ነበር።


“ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፤ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት!


በም​ድ​ርም ከሚ​ሰማ ወሬ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ ልባ​ች​ሁም የዛለ አይ​ሁን፤ በአ​ንድ ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ በሌ​ላው ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ላይ ግፍ ይነ​ግ​ሣል፤ አለ​ቃም በአ​ለቃ ላይ ይነ​ሣል።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚ​ለ​ውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አት​በሉ፤ መፈ​ራ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።


ከሚመጣብህም አስደንጋጭ ነገር፥ ከሚመጣውም የክፉዎች ሰዎች አደጋ አትፈራም፤


ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤


ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ነፍ​ሴን አት​ው​ሰ​ዳት፤ ክፋ​ትም በል​ባ​ቸው እያለ ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ጋር ሰላ​ምን ከሚ​ና​ገሩ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ጋር አት​ጣ​ለኝ።


ሞትን እን​ሞ​ታ​ለ​ንና፥ በም​ድ​ርም ላይ እንደ ፈሰ​ሰና እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ ውኃ እን​ሆ​ና​ለ​ንና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነፍ​ስን ይወ​ስ​ዳል። የተ​ጣ​ለ​ው​ንም ከእ​ርሱ ያርቅ ዘንድ ያስ​ባል።


“ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፤ በእ​ኔም እመኑ።


ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤


ብዙዎች ‘እኔ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements