Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ነገር ግን ‘ከሰው ነው’ እንበልን?” አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ‘ከሰው ነው’ ብንል …” ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ እውነተኛ ነቢይ እንደ ሆነ ይቈጥር ስለ ነበር ፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “ታዲያ፥ ከሰው ነው፤ እንበልን?” ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ እውነተኛ ነቢይ መሆኑን ያምኑ ስለ ነበር ፈሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ‘ከሰው ነው፥’ ብንልሳ?” ይህን እንዳይሉ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን በእርግጥ ነቢይ ነው ይሉ ስለ ነበር ፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ነገር ግን፦ ከሰው ነው እንበልን? አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።

See the chapter Copy




ማርቆስ 11:32
15 Cross References  

ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ።


ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስላዩት ፈሩአቸው።


ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።


ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።


ብዙ​ዎ​ችም ወደ እርሱ ሄደው፥ “ዮሐ​ንስ ምንም ያደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የለም፤ ነገር ግን ዮሐ​ንስ ስለ​ዚህ ሰው የተ​ና​ገ​ረው ሁሉ እው​ነት ሆነ” አሉ።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።


ያን ጊዜም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎች ሊይ​ዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነ​ርሱ እንደ መሰለ ዐው​ቀ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ፈሩ​አ​ቸው።


ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር።


ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።


እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ “‘ከሰማይ ነው፤’ ብንል ‘እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤


ለኢየሱስም መልሰው “አናውቅም፤” አሉት ኢየሱስም “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም፤” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements