Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 1:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 “ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ፤” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “ለማንም አንድ ነገር እንኳ እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 “ለማንም አንድ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 “ይህን ነገር ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝቡም ምስክር እንዲሆን ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ፤” ብሎ አዘዘው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 1:44
9 Cross References  

ባያ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ ካህን ሂዱና ራሳ​ች​ሁን አስ​መ​ር​ምሩ” አላ​ቸው፤ ሲሄ​ዱም ነጹ።


ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።


እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።


የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በመ​ታ​ገ​ሣ​ች​ንና መጻ​ሕ​ፍ​ትን በመ​ታ​መ​ና​ችን ተስ​ፋ​ች​ንን እና​ገኝ ዘንድ እና ልን​ማ​ር​በት ተጻፈ።


ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገር ከለ​ከ​ለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስ​ህን ለካ​ህን አስ​መ​ር​ምር፤ ምስ​ክ​ርም ይሆ​ን​ባ​ቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባ​ህን አቅ​ርብ” ብሎ አዘ​ዘው።


በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አሰናበተው፤


ከዚ​ህም በኋላ፤ የሻ​ለ​ቃው፥ “ይህን ነገር ለእኔ መን​ገ​ር​ህን ለማ​ንም እን​ዳ​ት​ገ​ልጽ” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements