Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 9:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ። እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ ሳሉ፥ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ፦

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ታላቅ ኀይል በማየታቸው ተገረሙ፤ ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ነገር በመደነቅ ላይ ሳሉ እርሱ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥

See the chapter Copy




ሉቃስ 9:43
14 Cross References  

በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይገድሉትማል፤


የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።


እር​ሱም “እም​ነ​ታ​ችሁ ወዴት አለ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ፈር​ተው ተደ​ነቁ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ውኃም ነፋ​ስም የሚ​ታ​ዘ​ዙ​ለት ይህ ማነው?” አሉ።


ሁሉም ተደ​ነቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እጅ​ግም እየ​ፈሩ፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን” አሉ።


ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።”


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሁሉ ስለ ተያ​ዘው ዓሣ ተደ​ን​ቀው ነበ​ርና።


ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱ ራሳቸው ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤


ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።


በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements