Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 9:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ልጁም በመምጣት ላይ ሳለ ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው፤ ልጁንም ለአባቱ መልሶ ሰጠው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ልጁም ወደ ኢየሱስ በቀረበ ጊዜ ጋኔኑ በመሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸው፤ ልጁንም ፈውሶ ለአባቱ ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 9:42
12 Cross References  

የሞ​ተ​ውም ተነ​ሥቶ ተቀ​መጠ፤ መና​ገ​ርም ጀመረ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት።


ስለዚህ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ! ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”


እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤ ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል።


ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።


ግያ​ዝ​ንም ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። ጠራ​ትም፤ ወደ እር​ሱም በገ​ባች ጊዜ፥ “ልጅ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ውሰጂ” አላት።


እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው።


ኤል​ያ​ስም ብላ​ቴ​ና​ውን ይዞ ከሰ​ገ​ነቱ ወደ ቤት አወ​ረ​ደው፥ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፥ “እነሆ፥ ተመ​ል​ከች ልጅሽ ድኖ​አል” አለ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “የማ​ታ​ምን ከዳ​ተኛ ትው​ልድ፥ እስከ መቼ ከእ​ና​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼስ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ? ልጅ​ህን ወደ​ዚህ አም​ጣው” አለው።


እነ​ር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ባደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ሁሉ ሲደ​ነቁ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው።


ሃያ አም​ስት ወይም ሠላሳ ምዕ​ራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በባ​ሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታን​ኳዉ በቀ​ረበ ጊዜም ፈሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements