ሉቃስ 9:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ከዚህም በኋላ ከእርሱ ሲለዩ ጴጥሮስ ጌታችን ኢየሱስን፥ “መምህር፥ ሆይ፥ እዚህ ብንኖር ለእኛ መልካም ነው፤ ሦስት ሰቀላዎችንም እንሥራ፤ አንዱን ለአንተ፥ አንዱንም ለሙሴ፥ አንዱንም ለኤልያስ” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ከእርሱም ሁለቱ ሰዎች በተለዩ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ “አቤቱ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ፥ አንድም ለሙሴ፥ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤” አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ሁለቱ ሰዎች ከኢየሱስ ተለይተው በሄዱ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ!” አለው፤ ጴጥሮስ ይህን ሲናገር የሚለውን አያውቅም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር። See the chapter |