Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 8:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ቀር​ባም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆመ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ ዳሰ​ሰች፤ ያን​ጊ​ዜም የደ​ምዋ መፍ​ሰስ ቆመ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 እርስዋ ወደ ኢየሱስ መጥታ ከበስተኋላው ቀረበችና የልብሱን ጫፍ ነካች፤ ወዲያውኑ ደምዋ መፍሰሱን አቆመ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 8:44
15 Cross References  

“በም​ት​ለ​ብ​ሰው በል​ብ​ስህ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ዘርፍ አድ​ርግ።


ከል​ብሱ ዘር​ፍና ከመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያዉ ጫፍ ቈር​ጠው እየ​ወ​ሰዱ በድ​ው​ያኑ ላይ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ይፈ​ወሱ ነበር፤ ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስ​ትም ይወጡ ነበር።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና።


እጁ​ንም በላ​ይዋ ጫነ፤ ያን​ጊ​ዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነ​ችው።


በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር።


በገባበትም ስፍራ ሁሉ፥ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን፥ በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።


ኢየሱስም አዘነላቸውና ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ፤ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


ጴጥ​ሮ​ስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያር​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ ድው​ዮ​ችን በአ​ል​ጋና በቃ​ሬዛ እያ​መጡ በአ​ደ​ባ​ባይ ያስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው ነበር፤


እነሆም ከዐሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማን ዳሰ​ሰኝ?” አለ፤ ሁሉም ካዱ፤ ጴጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሰው ይጋ​ፋ​ህና ያጨ​ና​ን​ቅህ የለ​ምን? አንተ ግን ማን ዳሰ​ሰኝ? ትላ​ለህ” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements