Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 8:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እርሱ ግን፥ “ወደ ቤትህ ተመ​ል​ሰህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ል​ህን ታላቅ ነገር ሁሉ ተና​ገር” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው። እር​ሱም ሄዶ በከ​ተ​ማዉ ሁሉ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ሁሉ ተና​ገረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ወደ ቤትህ ተመልሰህ፣ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላቅ ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላቅ ነገር በከተማው ሁሉ በይፋ እየተናገረ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 “ወደ ቤትህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ተናገር።” እርሱም በመላው ከተማ ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት እየሰበከ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “ወደ ቤትህ ሂድና እግዚአብሔር ያደረገልህን ሁሉ ተናገር!”፤ ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ትልቅ ነገር በከተማው ሁሉ እየተናገረ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ ተመለስ፥ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ንገር ብሎ አሰናበተው። ኢየሱስም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት በከተማው ሁሉ እየሰበከ ሄደ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 8:39
13 Cross References  

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው።


እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።


ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው።


ኢየሱስም አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን “ወደ ቤትህ ወደ ቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው፤” አለው።


ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ሕዝቡ በአ​ን​ድ​ነት ተቀ​በ​ሉት፤ ሁሉ ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበ​ርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements