Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፤ “ወደ በረሓ የወጣችሁት ምን ልታዩ ነው? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸንበቆ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የዮሐንስ መልክተኞችም ከሄዱ በኋላ፥ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸምበቆን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ እያለ ይናገር ጀመር፦ “ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የዮሐንስ መልክተኞችም ከሄዱ በኋላ፥ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ይናገር ጀመር እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ?

See the chapter Copy




ሉቃስ 7:24
14 Cross References  

እን​ግ​ዲህ በሽ​ን​ገ​ላ​ቸው ያስቱ ዘንድ በሚ​ተ​ና​ኰሉ ሰዎች ተን​ኰል ምክ​ን​ያት በት​ም​ህ​ርት ነፋስ ሁሉ ወዲ​ያና ወዲህ እየ​ተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ም​ንና እየ​ተ​ን​ሳ​ፈ​ፍን ሕፃ​ናት አን​ሁን።


ሐናና ቀያ​ፋም ሊቃነ ካህ​ናት በነ​በ​ሩ​በት ወራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድረ በዳ ወደ ዘካ​ር​ያስ ልጅ ወደ ዮሐ​ንስ መጣ።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።


እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ! ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዐመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤


ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውሃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።


እር​ሱም፥ “ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ እንደ ተና​ገረ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ እያለ በም​ድረ በዳ የሚ​ሰ​ብክ የዐ​ዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ።


እንደ ውኃ የሚ​ዋ​ልል ነው፤ ኀይል የለ​ውም፤ ወደ አባቱ መኝታ ወጥ​ቶ​አ​ልና፤ ያን ጊዜ የወ​ጣ​በ​ትን አልጋ አር​ክ​ሶ​አ​ልና።


በእ​ኔም የማ​ይ​ሰ​ና​ከል ብፁዕ ነው።”


ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements