ሉቃስ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 መልእክተኞችም ወደ እርሱ ደርሰው፥ “የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የምናደርገው ሌላ አለ? ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ “መጥምቁ ዮሐንስ፣ ‘ይመጣል የተባለልህ አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብሎ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ሰዎቹም ወደ እርሱ ቀርበው እንዲህ አሉ፦ “መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ወደ አንተ ላከን፦ ‘የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 እነርሱም ወደ ኢየሱስ ሄደው “ ‘ያ ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብላችሁ ጠይቁት ሲል መጥምቁ ዮሐንስ ወደ አንተ ልኮናል፥” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ሰዎቹም ወደ እርሱ መጥተው፦ መጥምቁ ዮሐንስ፦ የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላውን እንጠብቅ? ብሎ ወደ አንተ ላከን አሉት። See the chapter |