Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 6:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዕውር ዕው​ርን ሊመራ ይች​ላ​ልን? ሁለ​ቱስ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድቁ የለ​ምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ደግሞም ይህን ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ ተያይዘው ጕድጓድ አይገቡምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እርሱም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “ዐይነ ስውር ዐይነ ስውርን መምራት ይችላልን? ሁለቱም በጉድጓድ አይወድቁምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “ ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? እንዲህማ ቢያደርግ ሁለቱም ተያይዘው በጒድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ምሳሌም አላቸው፦ ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ በጕድጓድ አይወድቁምን?

See the chapter Copy




ሉቃስ 6:39
14 Cross References  

ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።


ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤


እናንተ እባቦች! የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?


አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ እፍ​ረ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚህ ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ርኩስ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ ውር​ደ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚ​ህም ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸው ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አንተ የዕ​ው​ሮች መሪ፥ በጨ​ለ​ማም ላሉት ብር​ሃን እንደ ሆንህ በራ​ስህ የም​ት​ታ​መን ከሆ​ንህ፥


በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው “እነሆ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements