Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 አንዱን ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህን አትከልክለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጉንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን እንኳ አትከልክለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 አንዱን ጒንጭህን በጥፊ ለሚመታህ፥ ሌላውንም ጒንጭህን እንዲመታ አዙርለት፤ ነጠላህን ለሚወስድብህ፥ እጀ ጠባብህንም ጨምረህ ስጠው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 6:29
15 Cross References  

በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


የሚ​ገ​ዙ​አ​ች​ሁ​ንና የሚ​ቀ​ሙ​አ​ች​ሁን፥ መባያ የሚ​ያ​ደ​ር​ጓ​ች​ሁ​ንና የሚ​ታ​በ​ዩ​ባ​ች​ሁን፥ ፊታ​ች​ሁ​ንም በጥፊ የሚ​መ​ት​ዋ​ች​ሁን ትታ​ገ​ሡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁና።


እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?


ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።


በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፤ ሌሎችም በጥፊ መትተው “ክርስቶስ ሆይ! በጥፊ የመታህ ማን ነው?


ጕን​ጩን ለሚ​መ​ታው ይሰ​ጣል፤ ስድ​ብ​ንም ይጠ​ግ​ባል።


ጀር​ባ​ዬን ለግ​ር​ፋት፥ ጕን​ጬ​ንም ለጽ​ፍ​ዐት ሰጠሁ፤ ፊቴ​ንም ከም​ራቅ ኀፍ​ረት አል​መ​ለ​ስ​ሁም።


እኛ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ እን​ራ​ባ​ለን፤ እን​ጠ​ማ​ለን፤ እን​ራ​ቈ​ታ​ለን፤ እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ማረ​ፊ​ያም የለ​ንም፤ እን​ደ​በ​ደ​ባ​ለ​ንም።


ሸፍ​ነ​ውም ፊቱን በጥፊ ይመ​ቱት ነበር፤ “ፊት​ህን በጥፊ የመ​ታህ ማነው? ንገ​ረን” እያ​ሉም ይጠ​ይ​ቁት ነበር።


ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ግን ጳው​ሎ​ስን አፉን እን​ዲ​መ​ቱት በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን አዘዘ።


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


የካ​ህ​ና​ንም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም በጥፊ መታ​ውና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ከአ​ንተ ጋር ይና​ገር ዘንድ በምን መን​ገድ ከእኔ አለፈ?” አለው።


ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በደ​ኅና ወደ ቤቱ ከተ​መ​ለሰ እርሱ ሁሉን ይው​ሰ​ደው” አለው።


ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ሁሉ ስጥ፤ ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም እን​ዲ​መ​ልስ አት​ጠ​ይ​ቀው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements