Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በቍጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም እርስ በርስ ተወያዩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነርሱ ግን በቁጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስም ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን በጣም ተቈጥተው በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነርሱም ቍጣ ሞላባቸው፥ በኢየሱስም ምን እንዲያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተባባሉ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 6:11
16 Cross References  

ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ተበ​ሳጩ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋጩ፤ ሊገ​ድ​ሉ​አ​ቸ​ውም ወደዱ።


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


በየ​ም​ኵ​ራቡ ሁሉ የማ​ስ​ገ​ደጃ ማዘዣ አም​ጥቼ፥ በግድ የኢ​የ​ሱ​ስን ስም እን​ዲ​ሰ​ድቡ ዘወ​ትር መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንም ወደ ሌሎች ከተ​ማ​ዎች እያ​ሳ​ደ​ድሁ ከፋ​ሁ​ባ​ቸው።


ይህ​ንም ሰም​ተው ተበ​ሳጩ፤ ልባ​ቸ​ውም ተና​ደደ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋ​ጩ​በት።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


ከሸ​ን​ጎ​ውም ጥቂት ፈቀቅ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸ​ውና እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ?


ከዚህ በኋ​ላም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በገ​ሊላ ይመ​ላ​ለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድ​ርም ሊሄድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበ​ርና።


በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ።


የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤


እነርሱም “እንጀራ ባንይዝ ነው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።


እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ዙሮ ከተ​መ​ለ​ከተ በኋላ፦ ያን ሰው፥ “እጅ​ህን ዘርጋ” አለው፤ ሰው​ዬ​ውም ዘረ​ጋት፤ እጁም ዳነ​ችና እንደ ሁለ​ተ​ኛ​ይቱ ሆነች።


በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤


ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements