Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 4:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሁሉም ተገረሙ፤ እርስ በርሳቸውም፣ “ለመሆኑ ይህ ትምህርት ምንድን ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም እኮ ይወጣሉ” ተባባሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ሁሉም ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፦ “ይህ ቃል ምንድነው? በሥልጣንና በኃይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፥ እነርሱም ይወጣሉ፤” እያሉ ይነጋገረሩ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ሁሉም በመደነቅ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ምን ዐይነት ቃል ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዛል፤ እነርሱም ታዘው ይወጣሉ፤” ተባባሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ሁሉንም መደነቅ ያዛቸው፥ እርስ በርሳቸውም፦ ይህ ቃል ምንድር ነው? በሥልጣንና በኃይል ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛልና፥ ይወጡማል ብለው ተነጋገሩ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 4:36
10 Cross References  

አነ​ጋ​ገ​ሩም በት​እ​ዛዝ ነበ​ርና ትም​ህ​ር​ቱን ያደ​ንቁ ነበር።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ያለ መጠንም ተገረሙና “ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል፤” አሉ።


ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።


ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ድዳው ተናገረ። ሕዝቡም “እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም፤” እያሉ ተደነቁ።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እረ​ኞቹ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸ​ውን አደ​ነቁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements