Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የነቢዩም የኢሳይያስ ጥቅል ብራና ተሰጠው፤ ጥቅሉንም በዘረጋው ጊዜ፥ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ተሰጠው፤ መጽሐፉንም በገለጠ ጊዜ፥ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17-19 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 4:17
9 Cross References  

ኦሪ​ት​ንና ነቢ​ያ​ትን ካነ​በቡ በኋ​ላም የም​ኵ​ራቡ አለ​ቆች፥ “እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለሕ​ዝብ ሊነ​ገር የሚ​ገ​ባው የም​ክር ቃል እንደ አላ​ችሁ ተና​ገሩ” ብለው ላኩ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​ያ​ቸው፤ የሰ​ማይ ጭፍ​ራን ያመ​ል​ኩም ዘንድ ተዋ​ቸው፤ የነ​ቢ​ያት መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፤ ‘እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በውኑ በም​ድረ በዳ ሳላ​ችሁ አርባ ዐመት ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ልኝ ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት አለን?


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ግን እር​ሱን አላ​ወ​ቁም፤ የነ​ቢ​ያት መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ ሲያ​ነቡ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ ነገር ግን ይሙት በቃ ፈረ​ዱ​በት፥ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ፈጸ​ሙ​በት።


እርሱ ራሱ ዳዊት በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘ጌታ ጌታ​ዬን በቀኜ ተቀ​መጥ፥


ወደ አደ​ገ​በት ወደ ናዝ​ሬ​ትም ሄደ፤ በሰ​ን​በት ቀንም እን​ዳ​ስ​ለ​መደ ወደ ምኵ​ራብ ገባ፤ ሊያ​ነ​ብም ተነሣ።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት።


አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴና ነቢ​ያት አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱን ይስሙ’ አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements